መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 26፤2014-የብራዚል ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ በአንጀት መዘጋት ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ

የብራዚል ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ በአዲስ ዓመት እለት ከታመሙ በኋላ በአንጀት መዘጋት ሆስፒታል ገብተዋል።ፕሬዚዳንቱ በሆስፒታል አልጋ ላይ እንደተኙ በትዊተር ገፃቸው ላይ በፎቶ አስደግፈው ባጋሩት መልዕክት ዶክተሮች በአፍንጫዬ ቱቦ አስገብተው እየመረመሩ ይገኛል፤ የቀዶ ጥገና ህክምና ሊያደርጉልኝ ይችላል ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱን የሚመረምሩ የህክምና ባለሙያዎች በትላንትናው እለት በሰጡት መግለጫ የጤናቸው ሁኔታ መሻሻል አሳይቷል ብለዋል። የ66 አመቱ ቦልሶናሮ እ.ኤ.አ በ2018 በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ሆዳቸው ላይ በስለት ገዳት ከደረሰባቸው በኋላ ለበርካታ ጊዜያት ሆስፒታል ገብተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *