
በሞሪሺየስ የአየር መንገድ አውሮፕላን የመጸዳጃ ቤት ውስጥ የተጣለ ጨቅላ ህጻን ማግኘታቸዉን የበረራ ሰራተኞች አስታዉቀዋል፡፡ በአውሮፕላኑ ውስጥ የማዳጋስካር ዜግነት ያላት የ20 አመት ሴት በቁጥጥር ስር ዉላለች፡፡
ከማዳጋስካር የመጣው የኤር ሞሪሸስ አይሮፕላን በአዲስ ዓመት እለት በሰር ሲዉሳጉር ራምጉላም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሰ በኃላ የኤርፖርቱ መኮንኖች መደበኛ የጉምሩክ ፍተሻ ሲያደርጉ ጨቅላ ህጻኑን አግኝተዋል፡፡ህፃኑን በፍጥነት ወደ ህዝብ ሆስፒታል ለህክምና እንደተወሰደ ተሰምቷል፡፡
የልጁ እናት መሆኗን የተጠረጠረችው ግለሰብ ፣ ልጁ መጀመሪያ ላይ የሷ አለመሆኑን የካደች ቢሆንም መውለዷን የሚያረጋግጥ የህክምና ምርመራ ተደርጎላታል፡፡በአሁኑ ወቅት በሆስፒታሉ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ትገኛለች፡፡
እናቲቱም ሆኑ ሕፃኑ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡ከሆስፒታል ከወጣች በኋላ አዲስ የተወለደ ልጅን በመጣል በሚል ወንጀል ትጠየቃለች፡፡
በስምኦን ደረጄ