መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 27፤2014-የደሴ ከተማ ነዋሪዎች የኑሮ ወድነት ፈተና እንደሆነባቸው ተናገሩ

የደቡብ ወሎ ዞን መቀመጫ በሆነችው የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ሽብርተኛው የህወኃት ቡድን ባደረሰው ጥፋት የተነሳ ኑሮ እየፈተነን ነው ሲሉ በተለይ ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ከትራንስፖርት ዋጋ መናር ጀምሮ ጥራጥሬ ፣ጤፍ እንዲሁም ሌሎች መገልገያዎች በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ለመመለስ እንዳይችሉ እንዳደረጋቸው አንስተዋል።

ከደሴ ወደ ኩታበር እንዲሁም ወደ ሃይቅ ያለው ትራንስፖርት ያልተገባ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በባጃጃ እንቅስቃሴ የሚደረግባቸው የቅርብ ርቀት ጉዞ ዋጋ ጭማሪ ማሳየታቸውን ያስረዳሉ ፡፡ሽሮ በሳህን ከ80 እሰከ 90 ብር ፣ በርበሬ በኪሎ 300 ብር፣ ከሰል 320 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች እርዳታ ለማግኘት እየተቸገሩ ሲሆን የሚሰጠውም እርዳታ በቂ አለመሆኑን ለብስራት ሬዲዮ ቅሬታቸን ያቀረቡ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ቅሬታውን ተከትሎ ምላሽ እንዲሰጡ ጣቢያችን ያናገርናቸው የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል ቅሬታው አግባብ ነው ያሉ ሲሆን በትራንስፖርት ረገድ በነዳጅ መጨመር ምክንያት ችግሩ መፈጠሩን አንስተዋል፡፡ ያለውን ክፍተት ለማስተካከል የደሴ ትራንስፖርት ቢሮ ባወጣው ታሪፍ እንዲንቀሳቀሱ ስራ እተሰራ ሲሆን ከታሪፍ በላይ የሚጭኑት ላይ እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል፡፡ሆኖም ግን በእርዳታ በኩል ለተጎጂዎች በሙሉ ማዳረስ እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

የነጋዴው መዘረፍ ችግሩን ያባባሰው ሲሆን በአቅርቦት ረገድ ያለውን ችግር ለመፍታት አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ ቦታዎች ግብዐት ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል ጨምረው ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *