የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አማካኝነት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የታደሱ እና በአዲስ የተገነቡ 496 ቤቶችን በዛሬው ዕለት ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል፡፡
ባለፉት ወራት በክረምት የበጎ ቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር የተጀመሩ ከ315 ቤቶችን እድሳት በማድረግ እና ፣181 አዲስ የቀበሌ ቤቶችን በመገንባት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩና አቅመ ደካሞች ነው የመኖሪያ ቤቶቹ የተላለፉት፡፡
መረዳዳት እና መተጋገዝ የኢትዮጵያዊያን ባህል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ በክረምት በጎ ፍቃድ መርሃግብርም የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው በተለያ የበጎ አድራጎት ሥራ የተሳተፉ ተቋማት እና ግለሰቦች እንዲሁም ወጣቶች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቤታቸው ፈርሶ በተለይ በክረምት ወራት መኖር እስኪከብዳቸው ሲቸገሩ የቆዩ ዜችን ቤት በማደስ የተቸገሩትን መርዳት ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ በጎ ተግባር ነው ብለዋል፡፡
በክረምት የተለያዩ ተቋማትን እና በጎ ፈቃደኛን በማስተባር ከ2ሺ በላይ ቤቶችን ለማደስ በእቅድ ተይዞ እስካሁን 2ሽህ 5 መቶ ቤቶችን ማደስና መገንባት እንደተቻለም ከንቲባዋ መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ አጠቃላይ እስካሁን ከ595 በላይ ቤቶችን በአዲስ በመገንባትና የወደቁ ቤቶችን በማደስ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ለከተማችን ነዋሪዎች፣ለአቅመ ደካሞች እና ለዘማች ቤተሰቦች ርክክብ ተደርጓል፡፡