መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 30፤2014-በሰሜናዊ ፓኪስታን በከባድ በረዶ መኪናቸው ከተያዘባቸው ሰዎች መካከል ቢያንስ የ21ዱ ህይወት አለፈ❗️

በሰሜናዊ ፓኪስታን በከባድ በረዶ መኪናቸው ከተያዘባቸዉ መካከል ቢያንስ የ21 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡የፓኪስታን ወታደሮች በኮረብታ ላይ የምትገኘውን እና የሙሬ ከተማ አቅራቢያ በበረዶዉ የተያዙ ሰዎችን ለመታደግ እየሰሩ እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

በከባድ ጎርፉ የተነሳ 1,000 የሚጠጉ ተሽከርካሪዎች በጎዳና ላይ መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ የፓኪስታን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ ራሺድ ተናግረዋል።ሙሬ ከዋና ከተማው ኢስላማባድ በስተሰሜን የሚገኝ ተራራማ ስፍራ ነው። የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት በበረዶው ምክንያት ቱሪስቶች ከአካባቢዉ እንዲወጡ መደረጋቸዉን ዘግበዋል፡፡

ከወትሮው በተለየ መልኩ ከባድ የበረዶ ዝናብ ለማየት ከ100,000 በላይ ተሸከርካሪዎች ወደ ሙሬ ተጉዘዋል። ይህም በከተማዋ በሚገቡ እና በሚወጡት መንገዶች ላይ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ እንዲፈጠር ማድረጋቸዉን የፓኪስታን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡

ፖሊስ እንዳስታወቀው ቢያንስ ስድስት ሰዎች በመኪናቸው ውስጥ እንዳሉ በበረዶዉ ተይዘዉ ህይወታቸዉ አልፏል፡፡ ነገር ግን ሌሎች እንዴት እንደሞቱ እስካሁን የተነገረ መረጃ የለም፡፡

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን በቱሪስቶች ላይ የደረሰዉን አሳዛኝ ሞት እንዳስደነገጣቸዉ ገልጸዋል፡፡ካን በትዊተር ገፃቸው ላይ አደጋዉን ለመከላከል ጠንካራ ስራ እንዲሰራ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *