መደበኛ ያልሆነ

ጥር 2፤2014-በኒውዮርክ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ

በኒውዮርክ የመኖሪያ ህንጻ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ 19 ሰዎች 9 ህጻናትን ጨምሮ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡የኒውዮርክ ከንቲባ ኤሪክ አዳምስ እንደተናገሩት ሌሎች 32 ሰዎች በደረሰባቸዉ ጉዳት ወደ ሆስፒታል መግባታቸዉን ተናግረዋል

የእሳት አደጋ መከላከያ ቢሮ ኮሚሽነር ዳንኤል ኒግሮ ባለ 19 ወለል ባለዉ ህንጻ ላይ በእያንዳንዱ ፎቅ ላይ ተጎጂዎችን ማግኘታቸውን ገልፀው ጭሱ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ነው ብለዋል።ለኤንቢሲ የዜና ወኪል እንደተናገሩት የሟቾች ቁጥር በኒውዮርክ ለ30 ዓመታት ከተመዘገበዉ አደጋ እጅግ የከፋ ነው ብለዋል።

የዚሁ አደጋ መድረስ የተሰማዉ ከቀናት በፊት በፊላደልፊያ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 12 ሰዎች ስምንት ህጻናትን ጨምሮ መሞታቸዉ ከተነገረ በኃላ ነዉ፡፡የእሁዱ ቃጠሎ የተነሳው በብሮንክስ አፓርትመንት ብሎክ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ፎቅ ላይ እንደሆነ የመንግስት ባለስልጣናት አስታዉቀዋል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *