መደበኛ ያልሆነ

ጥር 3፤2014-በአለም ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሳማ የተወሰደ ልብ ንቅለ ተከላ ለሰዉ ልጅ ተሰጠ

በጄኔቲክ ከተሻሻለው የአሳማ ልብ ንቅለ ተከላ የተደረገ አንድ አሜሪካዊ በአለም የመጀመሪያው ሰው ሆኗል። በባልቲሞር ለ57 ዓመቱ ዴቪድ ቤኔት ሰባት ሰአታት በፈጀ ሂደት ንቅለ ተከላዉ የተከናወነ ሲሆን ከህክምናዉ ከሶስት ቀናት በኋላ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ዶክተሮች ተናግረዋል፡፡

ንቅለ ተከላው የቤኔትን ህይወት የማዳን የመጨረሻ ተስፋ ተደርጎ ተወስዶ ነበር፡፡ከቀዶ ጥገናው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቤኔት ወይ ሞት አልያም ይህንን ንቅለ ተከላ እንደሚያደርጉ ተናግረዉ ነበር፡፡በጨለማ ውስጥ የተተኮሰ ጥይት እንደሆነ አውቃለሁ ነገር ግን የመጨረሻው ምርጫዬ ነበረ ብለዋል፡፡

በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ማእከል ዶክተሮች ቤኔት ህይወታቸዉ ሊያልፍ ይችላል በሚል ከንቅለ ተከላዉ በፊት በአሜሪካ የህክምና ተቆጣጣሪ ልዩ ፍቃድ ተሰጥቷቸዉ ነበር፡፡ንቅለ ተከላውን ላከናወነው የህክምና ቡድን የዓመታት የጥናት ዉጠየት መጨረሻዉን የሚያመለክት ሲሆን በአለም ዙሪያ የሰዉ ልጅ ህይወት ሊለውጥ እንደሚችል ታምኖበታል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *