
በሞሮኮ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ፕሮፌሰር የሆኑ መምህር ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንድሰጣችሁ ጾታዊ ግንኙነት ለማድረግ ጥያቄ በማቅረባቸዉ በሁለት አመት እስር እንዲቀጡ ዉሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡በሞሮኮ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከጾታ ትንኮሳ ጋር በተያያዘ እንዲህ ዓይነቱ ዉሳኔ ሲሰጥ የመጀመሪያው ነዉ፡፡
በካዛብላንካ አቅራቢያ በሚገኘው የሃሰን አንደኛ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት እኚሁ ፕሮፌሰር ከቀረበባቸዉ ክስ በተጨማሪ ጨዋነት በጎደለው ድርጊት ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።በመጪው ሀሙስ ተጨማሪ አራት መምህራን ከጾታዊ ትንኮሳ ቅሌት ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ባለፈው አመት በጋዜጠኞች አማካይነት በተማሪዎች እና በመምህራን መካከል ከጾታዊ ትንኮሳ ጋር የተያያዙ ዘገባ ይፋ ማድረጋቸዉን ተከትሎ ጉዳዩ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡በሞሮኮ የፆታዊ ትንኮሳ ጉዳዮች ለፍርድ ሲቀርብ ብዙም የተለመደ አይደለም፡፡
በስምኦን ደረጄ