መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2014-በኢትያጵያ አንድ ዶክተር ከዘጠኝ ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል ተባለ

በኢትዮጵያ የሚገኙ የሀኪሞች ቁጥር አነስተኛ በሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአሁን ወቅት አንድ ዶክተር ከዘጠኝ ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡የዓለም የጤና ድርጅት ከዚህ ቀደም ከሳህራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት አንድ ዶክተር ለአስር ሺ የሚል ዝቅተኛ መስፈርት ማስቀመጡ ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አንድ ሀኪም ለ9ሺ አራት መቶ ሰዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሀብት ልማት ክፍል ዋና ዳሬክተር አቶ አሰግድ ሳሙኤል ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡እንደ አቶ ሳሙኤል ማብራሪያ ይህ ቁጥር ከሳህራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ዘንድ ሲታይ መልካም የሚባል ቢሆንም ቁጥሩ ግን በቂ አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ከሰዓራ በታች ባሉ አገራት አንድ ሀኪም ለአስር ሺ የሚለውን ዝቅተኛ መስፈርት ለማስተካከል ጥናት እያደረገ ሲሆን በሚያወጣው አዲስ መስፈርት መሰረት ኢትዮጵያ ያለችበት ደረጃ ደግማ እንድታየው የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።ባደጉት የአለም ሀገራት አንድ ዶከተር እስከ አንድ ሺ ለሚደርሱ ሰዎች ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን እንደ የሀገራቱ እድገት ይህ ቁጥር ሊለያይ ይችላል።

በኢትዮጵያ ያሉ ዶክተሮች ቁጥር ከሳዓራ በታች ባሉ ሀገራት መስፈርት ሲመዘን ጥሩ ቢመስልም አነስተኛ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር በመረዳት የባለሙያዎቹን ቁጥር ከፍ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *