መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2014-በኢትዮጲያ በማህፀን በር ካንሰርየተነሳ በዓመት 5 ሺህ ሴቶች ለሞት ይዳረጋሉ

የማህፀን በር ካንሰር ፣ በካንሰር ምክንያት ከሚመጡና ከፍተኛ የጤና ችግር ከሚያጋልጡ ህመሞች ውስጥ ከጡት ካንሰር በመቀጠል ሁለተኛውን ስፍራ እንደሚይዝ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በእዚህ መነሻነትም በሽታውን ቀድሞ መከላከል የሚያስችል የክትባት ዘመቻ ሊካሄድ መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል ።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ ዘመቻውን አስመልክቶ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ።

በመግለጫው ጥር 4 የተጀመረው ይህው ዘመቻ እስከ ጥር 10 እንደሚቆይ ሃላፊው አንስተዋል ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2012 ዓ. ም ጀምሮ 3.6 ሚሊዮን ሴቶች የተከተቡ ሲሆን በአዲስ አበባ ደረጃ ደግሞ 150 ሺህ ለሚሆኑ ልጃገረዶች ክትባቱ እንደተሰጠ ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ ተናግረዋል ።

በዚህ ዓመትም ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ዘመቻ ዕድሜያቸው 14 ዓመት የሞላቸው ሴቶች በትምህርት ቤትና በተለያዩ ጤና ጣቢያዎች አማካይነት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በዘመቻውም 55 ሺህ 342 የሚሆኑ ሴቶችን ለመክተብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ በተጨማሪነት አንስተዋል ።

በማህፀን በር ካንሰር በየዓመቱ ከሚጠቁ 7 ሺህ ሴቶች ውስጥ 5 ሺህዎቹ ለሞት ይዳረጋሉ ሲሉ ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።

በናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *