መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2014-ናይጄሪያ ከሰባት ወራት በኋላ በትዊተር ላይ የጣለችዉን እገዳ አነሳች

ናይጄሪያ በትዊተር ላይ የጣለችውን እገዳ ከሰባት ወራት በኃላ ማንሳቷ ይፋ ተደርጓል፡፡የናይጄሪያ መንግስት ባለፈው ሰኔ ወር ትዊተርን ያገደዉ ሀገሪቱን ለመከፋፈል የመገንጠል አጀንዳ የሚያቀነቅኑ ሀይሎችን ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ እንደሚቀጡ በትዊተር ላይ የጻፉትን መልእክት የትዊተር ኩባንያ መሰረዙን ተከትሎ ነዉ፡፡

የናይጄሪያ የመንግስት ባለስልጣናት የማህበራዊ ሚዲያ የሆነዉ ትዊተር ከተገንጣዮቹ ጋር ወግኗል ሲሉ ከሰዋል።ነገር ግን ትዊተር ናይጄሪያ ውስጥ የቀጠናዉን ቢሮ መክፈትን ጨምሮ ቅድመ ሁኔታዎችን ከተስማማ በኋላ መንግስት እገዳውን እንደቀለበሰ ተሰምቷል፡፡

በትዊተር ላይ እገዳዉ መነሳቱ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛቷ ቀዳሚ በሆነችዉ ናይጄሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መድረኩን እንደገና እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል።አንዳንድ ተጠቃሚዎች ቨርቹዋል የግል ኔትወርኮችን (ቪፒኤን) በመጠቀም እገዳዉ በነበረበት ወቅት ይጠቀሙ ነበር፡፡

ባለፈው አመት የናይጄሪያ መንግስት የወሰደው እርምጃ በአለምአቀፍ ደረጃ የመናገር ነፃነት የሚገድብ በሚል ቅሬታን አስነስቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ትዊተር በበርካታ ናይጄሪያውያን ዘንድ ተወዳጅ ማህበራዊ መድረክ ሲሆን እንደ ማነቃቂያ መሳሪያ ሆኖ አገልግሏል። ለአብነትም የመብት ተሟጋቾች የናይጄሪያ ፖሊስን ጭካኔ በመቃወም በ #EndSars ሃሽታግ ንቅናቄ የአለምን ትኩረት በመሳብ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ተጠቅመውበታል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *