መደበኛ ያልሆነ

ጥር 6፤2014-በደብር ብርሃን ከተማ በነገዉ እለት ለሚከበረው የቅድስት ስላሴ አመታዊ ክብረ በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቃቸው ተገለፀ።

በደብረ ብርሃን ከተማ ጥር 7 ቀን ለሚከበረው የቅድስት ስላሴ አመታዊ ክብረ በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው እና በበዓሉ እለት ከ25ሺ በላይ ሰዎች እንደሚታደሙ የደብረ ብርሃን ከተማ ሰላምና የህዝብ ደህንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡በደብር ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ብቻ 303 የሚሆኑ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ታሪካዊና ኃይማኖታዊ ቅርሶች ያሉ በመሆናቸው የቅድስ ሰላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓልን ከማክበር ጎን ለጎን በከተማው የሚገኙ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ኃይማኖታዊ መስህብ ሀብቶችን መጎብኘት የሚቻል መሆኑን ተገልፆል፡፡

ክብረ በዓሉ ያለምንም ችግር እንዲከበር የፀጥታ ተቋሙ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ እና አስቀድሞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንደተሰሩ አቶ ዳንኤል እሸቴ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በከተማው በአሁኑ ወቅት አስተማማኝ ሰላም ያለ ሲሆን ማህበረሰቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡ ለዚህ አገልግሎትም 400 የሚሆኑ የከተማው ወጣቶች ተመልምለው የተዘጋጁ መሆናቸውን ተገልጿል፡፡

ከበዓላት ጋር ተያይዞ ለሚፈጠሩ ችግሮች ኮማንድ ፖስቱ ውሳኔ የሚሰጥባቸው ራሳቸውን የቻሉ 4 የምርመራ ቡድኖች ተዋቅረው እየተሰራ በመሆኑ ማህበረሠቡ በዓሉን ያለምንም ችግር በሠላም ማክበር የሚችል መሆኑን አቶ ዳንኤል እሸቴ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *