መደበኛ ያልሆነ

ጥር 9፤2014-ሰሜን ኮሪያ ሁለት የባልስቲክ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ሴኡል አስታወቀች

ሰሜን ኮሪያ በዚህ ወር ባደረገችው አራተኛ የጦር መሳሪያ ሙከራ ሁለት አጭር ርቀት የሚምዘገዘጉ ሚሳኤሎችን ወደ ባህር መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታዉቋል።ደቡብ ኮሪያ በዛሬዉ እለት እንዳስታወቀችዉ ሰሜን ኮርያ በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ ከሚገኘው ሱናን አየር ማረፊያ ሁለት ባልስቲክ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን በመግለጽ ነገር ግን ምን ያህል ርቀት እንደተጓዙ ግን መረጃ አልተሰጠም።

የጃፓን መንግስት ሙከራዉ መፈጸሙን ማረጋገጫ በመስጠት የቀጠናውን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ሲል ድርጊቱን አዉግዟል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ መንግስታቸው መረጃ ለመሰብሰብ እንዲሁም የመርከብ እና የአውሮፕላኖቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ የተቻለውን ሁሉ እንዲደረግ መመሪያ ሰጥተዋል።

የጃፓን የባህር ጠረፍ ጥበቃ በጃፓን ውሃ ዙሪያ ለሚጓዙ መርከቦች ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም።የባህር ዳርቻ ጥበቃው በኋላ ላይ እንደገለጸው የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል ቀድሞ ማለፉን በመግለጽ የት እንደሆነ ግን አይታወቅም ሲል ይፋ አድርጓል፡፡ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ሳምንት መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን በተገኙበት የሃይፐርሶኒክ መሳሪያ በተሳካ ሁኔታ መሞከሯን ማስታወቋ የሚታወስ ሲሆን ከ2022 ዓመት መጀመሪያ አንስቶ ተከታታይ ሙከራዎችን አድርጋለች።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *