
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ሳውዲ አረቢያ በውክልና የሚሄዱ ልኡካን መዘጋጀቱን ማሳወቁ የሚታወስ ሲሆን አሁንም ስራው አለቆሙን እና የቪዛ ሂደት ላይ እንዲገኙ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡
የልዑኩ አባላት የቪዛ ሂደት የሳውዲ አረቢያ መንግስት ፈቃድ የሚፈልግ በመሆኑ እስካሁን ሊዘገየው የቻለው በዚህ ምክንያት መሆኑን ያነሱት አምባሳደሩ ቪዛው እንደደርሰ ዛሬም ቢሆን ልዑኩ እንዲሄድ ይደረጋል ብለዋል።
ቡድኑ ከሃይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ሰዎች እንዲሁም የሚመለክታቸው አካላት ያሉበት ሲሆን በጋር የተዋቀረ ነው።አምባሳደር ዲና የስደት ተመላሾች ጉዳይ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ እንዳይሆን ከስር መሰረቱ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።
ቤተልሄም እሸቱ