መደበኛ ያልሆነ

ጥር 12፤2014-የቼክ ሪፐብሊክ ታዋቂ ዘፋኝ ሆን ብሎ በኮቪድ በመጠቃት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓ ተሰማ

የቼክ ሪፐብሊክ ታዋቂ ድምጻዊት ሆን ብላ ራሷን በኮቪድ ቫይረስ እንድትጠቃ በማድረግ ህይወቷ ማለፉን ወንድ ልጇ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል፡፡የ57 ዓመቷ ሃና ሆርካ በማህበራዊ ድህረ ገጿ ላይ በኮሮና ቫይረስ መጠቃቷን ይፋ ካደረገች ከሁለት ቀናት በኋላ ህይወቷ አለፏል።

ልጇ ጃን ሬክ እና ወላጅ አባቱ በቫይረሱ በተያዙበት ወቅት ሆን ብላ በቫይረሱ ስለመጠቃቷ ተናግሯል፡፡ሬክ እና ወላጅ አባቱ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሲሆን ሁለቱም በገና በዓል ሰሞን በኮቪድ ተይዘዋል፡፡። ነገር ግን ክትባቱን ያልወሰደችዉ ድምጻዊቷ ራሷን ለቫይረሱ ማጋለጥን በመምረጥ ከእነሱ ላለመራቅ እንደወሰነች ተናግሯል።

በእርሷ ፍልስፍና ከክትባት ይልቅ በኮቪድን መያዝን ትመርጥ እንደነበር በመግለጽ ይህ ስህተት ዋጋ እንዳስከፈላት ተናግሯል። ወደ ሲኒማ ቤቶች፣ ቡና ቤቶች እና ካፌዎች ጨምሮ ወደ በርካታ ማህበራዊ እና ባህላዊ ቦታዎች ለመግባት በቼክ ሪፑብሊክ የክትባት ወይም ከቫይረሱ ነጻ መሆኑን የሚያሳይ የቅርብ ሰዓታት ወረቀት ማቅረብ አስገዳጅ ነዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *