መደበኛ ያልሆነ

ጥር 13፤2014-በአሜሪካ አየር መንገድ አንዲት ተሳፋሪ ጭንብል(ማስክ) ለማድረግ ፍቃደኛ ባለመሆኑ የተነሳ በበረራ ላይ የነበረ አዉሮፕላን እንዲመለስ ሆነ

ከማያሚ ወደ ለንደን የሚጓዘው የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን አንዲት ተሳፋሪ የፊት ጭንብል ለማድረግ ፍቃደኛ ባለመሆኗ የተነሳ አዉሮፕላኑ ለመመለስ እንደተገደደ አየር መንገዱ አስታዉቋል።ንብረትነቱ የአሜሪካ አየር መንገድ የሆነዉና በረራ ቁጥሩ ኤ.ኤ.ኤል 38 የተሰኘዉ አዉሮፕላን 129 መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን ወደ ለንደን የሚያደርገዉን ጉዞ በማቋረጥ ማያሚ መመለሱ ታዉቋል፡፡

ለበረራዉ መስተጓጎል ምክንያት የሆነችዉ በ40ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ አንዲት ሴት እንደሆነች ከስፍራዉ የሚወጡ ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡ተጨማሪ ምርመራ በግለሰቧ ላይ የሚደረግ ሲሆን በአሜሪካ አየር መንገድ እንዳትጓዝ ከተከለከሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ መካተቷንም አየር መንገዱ አስታዉቋል።

በግለሰቧ እምቢተኝነት እሮብ እለት የተነሳዉ አዉሮፕላን አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ በድጋሚ ወደ ማያሚ ለመመለስ ተገዷል፡፡ወደ ለንደን ሄትሮው እያቀኑ የነበሩ ተሳፋሪዎች ሐሙስ እለት በሌላ በረራ በድጋሚ ቀጠሮ ተይዞላቸዉ መጓዝ ችለዋል።

በአብዛኛዉ ጭንብል ለማድረግ ፈቃደኛ ባልሆኑ መንገደኞችን የተነሳ አየር መንገዶች ባለፈው አመት ወደ 6,000 የሚጠጉ በረራዎች ላይ መስተጓጎል መከሰታቸውን የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር አስታውቋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *