መደበኛ ያልሆነ

ጥር 16፤2014-ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል በሁለት ቀናት ውስጥ የ21 ሆቴሎች የጥራት ደረጃ መረጋገጡ ተነገረ

የአዲስ አበባ ምግብ መድኃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በተያዘው ሳምንት ለሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለሚመጡ እንግዶች ማረፊያ የሚሆኑ ባለኮከብ ሆቴሎችን ጥራት ብቃትና ደህንነት ለማረጋገጥ ከጥር 13 እስከ ጥር 15 ድረስ የዘመቻ የቁጥጥር ስራ ተከናውኗል።

ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም ከ100 በላይ በሚሆኑ ሆቴሎች ላይ ቁጥጥር አድርጎ አንድ ሆቴል ምርቱ የተበላሸ የኬክ ዱቄት ሲጠቀም ተይዞ በከፊል ማሸጉን የባለስልጣኑ የምግብና የጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
ምሬሳ ሚደቅሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

መደበኛ የቁጥጥር ስራ ጊዜውን ጠብቆ እየተካሄደ ያለ ቢሆንም እንደዚህ ያለ ክስተት ሲኖር መደበኛ ስራዎችን ሳይጠብቅ በዘመቻ የሆቴሎችን የስራ ሂደት ፣የኮቪድ ጥንቃቄን እንደሚዳሰስ እና እንደሚሰራ ተገልጿል ።

የሆቴል ባለሀብቶችም ሆነ ባለሙያዎች እንግዶችን ለመቀበል በወሰዱት ፈቃድ ልክ ተቋማቸውን በማስተካከል እንግዶችን መቀበል አለባቸው ሲሉ አቶ ምሬሳ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *