መደበኛ ያልሆነ

ጥር 16፤2014-በሶሪያ ማረሚያ ቤት በደረሰ ጥቃትና ግጭት ቢያንስ 120 ሰዎች መገደላቸዉ ተሰማ

በሶሪያ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰ ጥቃት በአሜሪካ በሚደገፉ፣ የኩርድ ሀይሎች እና አይኤስ ተዋጊዎች መካከል በቀጠለው ጦርነት ቢያንስ 120 ሰዎች ተገድለዋል።መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው የሶሪያ የሰብአዊ መብቶች ታዛቢ ቡድን ሃሙስ በጀመረው ጥቃት ቢያንስ 77 የአይኤስ አባላት እና 39 የኩርድ ተዋጊዎች፣ የውስጥ ደህንነት ሃይሎች፣ የማረሚያ ቤት የጥበቃ አባላት እና የፀረ ሽብር ሃይሎች ተገድለዋል።

አይኤስ በማረሚያ ቤቱ መፍረስ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ አማቅ በተሰኘዉ የቡድኑ የፕሮፓጋንዳ ሚዲያ ላይ ይፋ አድርጓል።የአይኤስ ታጣቂዎች ወደ ማረሚያ ቤቱ ዘልቀው በመግባት የቡድኑን ጥቁር ባንዲራ በማዉለብለብ አባላቶቻቸዉን ለማስፈታት ጥቃት መፈጸም ጀምረዋል።

በኩርዲሽ የሚመራው የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ሃይል በአሜሪካ ወታደሮች እየታገዘ የአይኤስ ታጣቂዎች ላይ ከበባውን ማጠናከሩን እና 17 ወታደሮች እንደተገደሉበት አስታውቋል። ካመለጡት ታራሚዎች መካከል 104 የሚሆኑትን መልሰው መያዛቸዉን የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ገልጿል፡፡አይኤስ ጥቃቱን የጀመረዉ በማረሚያ ቤቱ በራፍ ላይ በተሸከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦንብ በማፈንዳት ነዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *