የአሜሪካ መንግስት ባስተላለፈዉ ዉሳኔ መሰረት መሰረታዉ ያልሆኑ ሰራተኞች አስፈላጊ ዩክሬንን እንዲለቁ ፍቃድ የሰጠ ሲሆን በዩክሬን የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች ሀገሪቱን ለመልቀቅ እንዲያስቡ አሳስቧል።በመግለጫው ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ማቀዷን የሚገልጽ ሪፖርት በዋሽንግተን በኩል ይፋ ሆኗል፡፡
ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር አቅዳለች ስትል አሜሪካ ይፋ ማድረጓን የሀሰት ክስ ስትል አጣጥላለች፡፡የአሜሪካ መንግስት በተጨማሪም ዜጎቹ ወደ ዩክሬን እና ሩሲያ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል፡፡ በዩክሬን እና ራሺያ በተፈጠረው ውጥረት የተነሳ በአሜሪካ ዜጎች ላይ ጥቃት ሊደርስ ይችላል ስትል ዋሽንግተን አስጠንቅቃለች፡፡
“ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዳቀደች ሪፖርቶች አሉ” ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ምክር ሀሳብ ሰጥቷል።አንድ የውጭ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ባለስልጣን ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ኤምባሲው አሁንም ሳይዘጋ ይቆያል ያሉ ሲሆን ከኋይት ሀውስ ግን ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች በመስጠት ወረራ ሊፈጸም ይችላል የሚል ሪፖርት መዉጣቱ አልተቋረጠም፡፡
በስምኦን ደረጄ