መደበኛ ያልሆነ

ጥር 16፤2014-የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት በቁጥጥር ስር ዋሉ

#Updated

የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ሮክ ማርክ ክርስቲያን ካቦሬ በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ መያዛቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።ፕሬዝዳንቱ የት እንዳሉ ግን የተብራራ መረጃ አልተሰጠም፡፡ሮይተርስ ሁለት የደህንነት ምንጮችን እና አንድ የምዕራብ አፍሪካ ዲፕሎማትን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በቁጥጥር ስር የዋሉት በጸጥታ ሃይሎች አማካይነት ነዉ፡፡

ቀደም ሲል በመዲናይቱ በሚገኘው የፕሬዚዳንቱ መኖሪያ አካባቢ የተኩስ ድምፅ የተሰማ ሲሆን ወታደሮቹ በወሰዱት እርምጃም በተለያዩ የጦር ሰፈሮች ውስጥ የተኩስ ድምጽ ነበር።በቡርኪናፋሶ በፕሬዝዳንት ቤተ መንግስት አካባቢ የተኩስ ድምፅ እንደነበር ተሰማ

በቡርኪናፋሶ ዋና ከተማ በሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግስት አካባቢ ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ከስፍራዉ የሚወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። በትላንትናዉ እለት በኦጋዱጉ በሚገኙ በርካታ የጦር ሰፈሮች የተኩስ ድምፅ የተሰማ ሲሆን፣ ወታደሮች ወታደራዊ አለቆቻቻዉ ከስልጣን እንዲባረሩ እና ታጣቂ ቡድኖችን ለመዋጋት ተጨማሪ ግብአት እንዲሰጣቸዉ ጠይቀዋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ወታደሮቹን ለመደገፍ አደባባይ የወጡ ሲሆን የቡርኪናፋሶ የመንግስት ባለሥልጣናት ዉጥረቱን ለመቆጣጠር የምሽት ሰዓት እላፊ አዋጅ እንዲያወጡ አስገድዷል፡፡መንግስት ቀውሱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግሯል።መፈንቅለ መንግስት ፈፅመዋል በሚል 11 ወታደሮች ከሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኃላ አዲስ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ነው መባሉን መንግስት ዉድቅ አድርጎታል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2015 ጀምሮ የምዕራብ አፍሪካን ግዛት ያወደመውን አማፂ ቡድን ማስቆም ባለመቻሉ በፕሬዚዳንት ሮክ ካቦሬ መንግስት ቅሬታ እየጨመረ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *