መደበኛ ያልሆነ

ጥር 17፤2014-ሰሜን ኮሪያ ሁለት የክሩዝ ሚሳኤሎችን መተኮሷ ሪፖርት ተደረገ

ሰሜን ኮሪያ በተያዘው ወር መጀመሪያ ላይ የተከለከሉ የባልስቲክ ሚሳኤል ሙከራዎችን ያደረገች ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ ሁለት የክሩዝ ሚሳኤሎችን ወደ ባህር መተኮሷን የደቡብ ኮርያ የዜና ወኪል ዮንሃፕ ወታደራዊ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። የደቡብ ኮሪያ ጦር በበኩሉ ሰሜን ኮርያ ያስወነጨፈችው የጦር መሳሪያን ምንነት እየገመገመ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ኤንኬ ኒውስ በበኩሉ የደቡብ ኮሪያን ወታደራዊ ባለስልጣንን ጠቅሶ ሁለት የክሩዝ ሚሳኤሎች መተኮሱን ዘግቧል።የደቡብ ኮርያ ጦር ጥምር ሃላፊዎች ስለ ሙከራው ወዲያውኑ ማረጋገጫ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል።

የክሩዝ ሚሳኤል ማስወንጨፍን በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት የሚከለከል አይደለም። ሆኖም ግን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ሰሜን ኮሪያ አለም አቀፍ ውግዘት ያስከተለባት አራት ዙር የባልስቲክ ሚሳኤል ሙከራዎችን አድርጋለች።

በሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሚመራው የሀገሪቱ ፖሊሲ አውጭ አካል የሀገሪቱን ወታደራዊ ሃይል ለማሳደግ እየተደረገ ባለው ጥረት “ለጊዜው የታገዱት” የኒውክሌር እና አህጉር አቀፍ የባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራዎችን እንደገና ለመጀመር እንደሚያስብ መግለፁብ የሰሜን ኮሪያ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *