
~ የቡርኪናፋሶ የመንግስት ግልበጣ የመሩት ፓውል ሄንሪ ሳንዳኦጎ ዳሚባ የሚባሉ ሲሆን በሀገሪቱ በሚደረገው የታጣቂዎችን ውጊያ በማክሸፍ ግንባር ቀደም ነበሩ።
~ የ41 ዓመቱ የመንግስት ግልበጣ መሪ ከዚህ ቀደም መፅሃፍ ፅፈው የነበረ ሲሆን ርዕሱም የምዕራብ አፍሪካ ጦር ሰራዊት እና ሽብርተኝነት እርግጠኛ ያልሆኑ ምላሾች የሚል ነበር።
~ በፈረንሳይ ወታደራዊ አካዳሚ በወንጀል ሳይንስ የሁለተኛ ዲግሪ ተቀብለዋል።
~ በ2015 የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በፅኑ የተቹ ቢሆንም ከሰባት ዓመት በኃላ ራሳቸው የመንግስት ግልበጣ ፈፅመዋል።
~ ስራቸውን የጀመሩት የፕሬዝዳንቱ የግል አጃቢ በመሆን ነበር።
ባለፉት 18 ወራት በአፍሪካ ስድስት ጊዜ ያህል የመንግስት ግልበጣ ተፈፅሟል።ሁለት ጊዜ በማሊ፣ጊኒ፣ቻድ፣ሱዳን እና በቡርኪናፋሶ ተፈፅሟል።
በስምኦን ደረጄ