መደበኛ ያልሆነ

ጥር 19፤2014-ባለፉት ስድስት ወራት የምግብ ጥራት ችግር የታየባቸው እና ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው የተገኙ 71 ተቋማቶች ታሸገዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በሁሉም ክፍለ ከተሞች በምግብ እና ጤና ነክ ተቋማት ዙሪያ የቁጥጥር ስራን ያከናውናል።

በዚህም መሰረት በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በ3,220 ተቋማት ላይ ባደረገው የቁጥጥር ስራ 71 ተቋማት መታሸጋቸውን የባለስልጣኑ የምግብና የጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምሬሳ ሚደቅሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ከነዚህም ውስጥ 69 የሚሆኑት ተቋማት የምግብ ጥራት እና የደህንነት ችግር ያለባቸው ሲሆኑ ሁለት ተቋማት ደግሞ በምግብ ክለሳ የታሸጉ ሲሆኑ ቂቤ እና ማርን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው በመገኘታቸው እርምጃው ተወስዶባቸዋል። ባእድ ነገሮችን ይዘው ከታሸጉ ተቋማት ውስጥ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በዋናነት ተጠቃሽ ነው፡፡

በተጨማሪም 98 የፅሁፍ እና 188 ተቋማቶች ላይ ደግሞ የቃል ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው እንዳሉ ተገልጿል ።ህብረተሰቡ ይህን መሰል ድርጊት አልያም አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮችን በሚመለከትበት ጊዜ በነፃ የስልክ መስመር 8064 ላይ በመደወል ለባለስልጣኑ ማሳወቅ እንዳለበት አቶ ምሬሳ ሚደቅሳ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *