መደበኛ ያልሆነ

ጥር 19፤2014-የአምባሳደሮች ሹመት በጥናት የተደረገ ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ ማብራሪያ በዛሬዉ እለት ለጋዜጠኞች ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫው ከተነሱ ነጥቦች መካከል ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ ለ27 አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤን በዚህ ሳምንት ስለመስጠታቸው አንዱ ነዉ፡፡

የተሰጠዉ ሹመት ከሌሎች ጊዜያት የሚለየው የብሄራዊ እና ሃገራዊ ጥቅምን የተሻለ ያደርጋሉ ፣ የለውጡን መንፈስ መሰረት ያደረገ ብሎም የለውጥ ግብ ያሳካሉ ተብሎ የታቀደ መሆኑን ለየት እንደሚያደርገው አምባሳደር ዲና ተናግረዋል፡፡አነስተኛ የሰው ሀያል በመጠቀም የስራ እና የሰራተኛው መመጣጠን እንዲኖር መሰራቱ ተገልጿል፡፡ከተሾሙት መካከል ነዋሪነታቸው በኢትዮጲያ ሆነዉ የሚሰሩ አሉበት የተባለ ሲሆን ይህም ከወጪ ቅነሳ አንጻር ጥቅሙ የጎላ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የስምሪቱ ሂደት ጥናት የተደረገበት ሲሆን በዘርፉ የሰሩና ከተለያዩ የስራ መስኮች የተካተቱበት እንደሆነም አምባሳደ ዲና መናገራቸዉን ብሰስራት ሬድዮ ሰምቷል፡፡

ቤቴልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *