
የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ በተደጋጋሚ ወደ ውጭ ሀገራት በሚያደርጉት ጉዞ የተነሳ ከተቃዋሚዎቻቸዉ ከፍተኛ ትችት እየተሰነዘረባቸዉ ይገኛል፡፡ሂቺሌማ በነሐሴ ወር ወደ ስልጣን ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ ዘጠነኛ የውጭ ጉዟቸውን ባሳለፍነዉ ረቡዕ አድርገዋል።
የቅርብ ቀን ጉዟቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ የነበረ ሲሆን በሁለት ቀናት ጉብኝታቸዉ ከአቻው ሲሪል ራማፎሳ ጋር ለመነጋገር እንዲሁም በመፅሃፍ ምረቃ ላይ ለመታደም እንደሆነም ተሰምቷል፡፡ነገር ግን ተቃዋሚው ሶሻሊስት ፓርቲ ከራማፎሳ ጋር ያደረጉት ውይይት የአክብሮት ጥሪ ተደርጎ ከተገለጸ በኋላ ጉዞውን አጠራጣሪ ነዉ ሲል ገልጿል፡፡
ከፕሬዝዳንት ራማፎሳ ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ በጉዞ ላይ ብቻ ከሆነ የፕሬዚዳንት ሂቺሌማ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉት ጉዞ ዓላማ ምንድን ነው? ከፕሬዚዳንት ራማፎሳ ጋር ያለው ስብሰባ ለግል ፍላጎታቸው መሸፈኛ ብቻ ነው ሲል የሶሻሊስት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ፍሬድ መሜምቤ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ጽፈዋል።ሂቺሌማ የተቃዋሚ ጎራ በነበሩበት ወቅት የቀድሞ የዛምቢያ ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ ውጭ ጉዞ ያበዛሉ በማለት ይተቹ የነበረ ቢሆንም ተመሳሳዩን ጥፋት በስድስት ወራት የስልጣን ዘመናቸዉ ደግመዉታል፡፡
ወጪን መቀነስ ከራሱ መጀመር አለበት ሲሉ ተቃዋሚዎቻቸዉ በመናገር ላይ ይገኛሉ፡፡ ሂቺሌማ ለቀረበባቸዉ ትችት ምላሽ ሲሰጡ “በልማት፣ በቀጠናው ሰላም እና ደህንነት ዙሪያ በኢኮኖሚያ ግንኙነታችንን ለማሳደግ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት ከራማፎሳ ጋር መደረጉን አረጋግጠዋል።በተጨማሪም በግሬግ ሚልስ የተፃፈውን እና ውድ ድህነት የተሰኘዉ መጸሀፍ ምርቃት ላይ መሳተፉቸዉን ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡
በስምኦን ደረጄ