
የተሻለ የትምህርት እና ጥሩ የቢሮ ስራ እድል መጨመሩን ተከትሎ የኦማን ሴቶች ቀደም ያሉ ወግ እና ትዳርን በተመለከተ ከመቼውም ጊዜ በላይ የእኩል የህይወት አጋርነት ጥያቄ በማቅረብ ላይ መሆናቸዉ ተሰምቷል፡፡ይፋዊ አኃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ2021 ከ3,800 በላይ ፍቺዎች የተመዘገቡ ሲሆን ይህም ከአንድ አመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ12 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
ከ10 አመት በፊት ከነበረዉ ጋር ሲነጻጸር በኦማን ፍቺ የሚጠይቁ ሴቶች ቁጥር መጨመሩን የመንግስት መረጃዎች ያመለክታሉ።ባህላዊ እሴቶች በፍጥነት እየተለዋወጡ ባሉበት ኦማን 67 በመቶ የሚሆኑ ፍቺዎች ባለፈው አመት በሴቶች የተጠየቁ መሆናቸውን ከስነ-ህግ እና ሀይማኖት ጉዳዮች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
‟ጋብቻ ሴቲቱ እና ባሏ አብረው ሕይወታቸውን የሚያቅዱበት እኩል ሽርክና መሆን አለበት፤ ባል በህይወትህ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ውሎችና ህጎቹ በፈቀደዉ መልኩ ሚስቱን ቢያስገድድ ይህ ጋብቻ አይደለም ”ስትል ከስምንት ዓመታት የትዳር ቆይታ በኃላ ፍቺ የፈጸመችዉ ፋትማ ተናግራለች።
በኦማን በ2021/22 የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ከተመዘገቡት ተማሪዎች አጠቃላይ ቁጥር 62 በመቶውን ድርሻ ያላቸዉ ሴቶች ናቸዉ። ከአሥር ዓመት በፊት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩት ሴቶች ቁጥር ከ39 በመቶው የበለጠ አልነበረም ።
በስምኦን ደረጄ