መደበኛ ያልሆነ

ጥር 23፣2014-በኬንያ በደረሰ ጥቃት ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ

በሰሜናዊ ኬንያ በተለምዶ ማታቱ ተብሎ በሚጠራው የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 9 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ክፉኛ መቁሰላቸዉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ይህ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ በድንበር አካባቢ ወደምትገኘው ማንዴራ እየተጓዘ የነበረ ሲሆን የታጣቂዎች ጥቃት ሰለባ ሆኗል፡፡

ከሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች የተገኙ የምስል ማስረጃዎች እንዳመላከቱት በመንገድ ላይ የተጠመደ ፈንጂ ላይ ተሸከርካሪዉ መጓዙን ተከትሎ አደጋዉ መድረሱን ከዉድመቱ አመላክተዋል፡፡ ለጥቃቱ እስካሁን ድረስ ሀላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም የአልሸባብ ታጣቂዎች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በማንዴራ እና አካባቢው በፖሊሶች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ ይገኛል፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው ዩናይትድ ስቴትስ እና ፈረንሳይን ጨምሮ በኬንያ የሚገኙ በርካታ የውጭ ኤምባሲዎች ዜጎቻቸውን በሀገሪቱ ሊደርስ ስለሚችሉ የሽብር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ከሰጡ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው።የኬንያ ፖሊስ በወቅቱ ደህንነትን የሚያረጋግጥ መግለጫ ማዉጣቱ ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *