
ኢትዮ ቴሌኮም የ2014 ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱ እንዳስታወቀው በቴሌብር የገንዘብ ዝውውር መሳካት አለበት ተብሎ ከታቀደው 88 በመቶውን ማሳካት የመቻሉን የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል ።
የቴሌብር ወኪሎች ቁጥር 46ሺህ የደረሰ ሲሆን ከ11ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ከቴሌብር ጋር አብረው መስራት መጀመራቸውንም በሪፖርታቸው ገልጸዋል።
አያይዘውም እንደገለጹት የቴሌብር አገልግሎትን አለም አቀፍ ሃዋላ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል።ከዚህም ባለፈ ከቴሌ ብር ጋር በጋራ ለመስራት የተፍራረሙ የውጪ ወኪሎች ስለመኖራቸውም ወ/ሪ ፍሬህይወት ታምሩ ጨምረው ተናግረዋል ።
አስራ አንድ ባንኮች ከቴሌብር ጋር እየሰራ ያሉ ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት 15.6 ሚሊዮን የገንዘብ ዝውውርም ተካሂዷል መባሉን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
በኤደን ሽመልስ