መደበኛ ያልሆነ

ጥር 23፣2014-የመጠጥ ውሃ ቱቦ ቆራርጠው በመኖሪያ ቤታቸው ደብቀው የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኦሮሚያ ክልል ወረጃርሶ ወረዳ የመጠጥ ውሃ ማስተላለፊ ቱቦዎችን በመኖሪያ ቤታቸው ደብቀው የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳዉ ፖሊስ አስታውቋል።

የወረጃርሶ ፖሊስ ከህብረተሱ በደረሰው ጥቋማ ባደረገው አሰሳ በሁለት ግለሰቦች መኖሪያ ቤት ውስጥ የውሃ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ተቋራርጠው በድብቅ ወደ አዲስ አበባ ሊጎጓዙ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል ምርመራ እና ፍትህ ማሰጠት የስራ ሂደት ባለቤት የሆኑት ዋና ሳጅን መሳይ ግርማ ለብስራት ሬዲዩ ተናግረዋል ።

በወረጃርሶ ወረዳ የመጠጥ እና ውሃ አገልግሎት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ጉግሳ ገመዳ ለቱሉ ሚልኪ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሀ አቅርቦት ለተያዘው ፕሮጀክት የውሃ ቱቦዎች በመስረቃቸው የመጠጥ ውሃ አገልግሎት አቅርቦቱ ላይ መቋረጡን መፈጠሩን ገልፀዋል።

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *