መደበኛ ያልሆነ

ጥር 24፣2014-ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከስጋ የወጪ ንግድ 59.43 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አገኘች

በ2014 በጀት አመት ባለፉት ስድስት ወራት በኢትዮጵያ የሥጋ የወጪ ንግድ ታሪክ ከፍተኛ አፈጻጸም መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ኢንዱሰትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ102.99 በመቶኛ ብልጫ ማሳየቱን በኢንስቲትዩቱ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደበሌ ለማ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ባለፈው 2013 አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ኢትዮጵያ ከዘርፉ 29.28 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘቷ ይታወሳል።እንደ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ደበሌ ማብራሪያ ከሆነ ከበግና ፍየል ስጋ የተገኘው ከፍተኛ ገቢ የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር አስተዋጽኦ ማድረጉ ጠቁመዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት 8880.5 ቶን የፍየልና የበግ ስጋ ወደ ውጪ ሃገራት በመላክ 50.3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። በድንበሮች አካባቢ ከእንስሳት ዝውውር ጋር ተያይዞ እያደረገ ያለው ቁጥጥር የተሻለ አፈጻጸም እንዲፈፀም አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተነስቷል።

ኢትዮጵያ 95 በመቶ የሚሆነውን የስጋ ምርቷንምላ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የምትልክ ሲሆን ሳውዲ አረቢያ እና ዱባይ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዙ ሀገራት ናቸው

በቅድስት ደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *