መደበኛ ያልሆነ

ጥር 24፣2014-የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት 14 አባላትን መጨመሩን አስታወቀ

ከአራት ዓመት በፊት ምስረተውን ያደረገው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው እለት በማካሄድ ላይ ይገኛል።በጉባኤው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት ሥራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ አማረ አረጋዊ የምክር ቤቱን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጻም ሪፖርት አቅርበዋል።

በኮሮና ወረርሽኝ የተነሳ ያለፈውን ዓመት ጉባኤ ባለመካሄዱ የተነሳ የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱ የሁለት ዓመቱን አቅርበዋል።ምክር ቤቱ በ2014 እቅዱ ዓመት የግልግል ዳኝነትና የእንባ ጠባቂ ስለ ምክር ቤት የህዝብ እውቅና እንዲኖር፣ የአባላት መዋጮን በተመለከተ፣የዲጂታል ሚዲያ የስነ ምግባር ደንብን ላይ እንደሚሰራም ጋዜጠኛ ታምራት ሀይሉ ተናግረዋል። በም/ቤቱ ጉባኤ ተጨማሪ 14 አባላት ላ የተቀላቀሉ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 60 አባላት በምክር ቤቱ ይገኛል።

በጉባኤው ላይም የክብር እንግዳ በመሆን የተገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ ለአገር ግንባታ ሚዲያ ያለውን ጉልህ ሚና በማንሳት ኢትዮጵያ ባሳለፈችው እና እያሳሳለፈች ባለችበት ከባድ ሁኔታዎች ሚዲያው የራሱን አዎንታዊ ሚና መጫወቱን አንስተዋል።

በጋዜጠኛ እና በፖለቲከኞች መካከል የሙያ መደበላለቅ ችግር መፍጠሩ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ገልጸዋል።ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ከምክር ቤቱ ጋር በጋራ በመሆን ችግሮቹን ለመቅረፍ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

የምክር ቤቱ አጋር በኢትዮጲያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ ተወካይ ንግግር አድርገዋል። ምክር ቤቱ በከሰዓት ውሎ በተጓደሉ የስራ አስፈፃሚ ምትክ ምርጫ፣የግልግል ዳኝነት የአሰራር ደንብና የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ላይ እንደሚወያይ ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *