በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ልዩ ቦታው መካኒሳ ታክሲ ማዞሪያ በደረሰ የእሳት አደጋ አንድ ሰው ላይ ቀላል ጉዳት ሲደርስ ሶስት ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የእሳት አደጋው የደረሰው ሌሊት ስምንት ሰዓት ሲሆን 600 ካሬ ሜትር ላይ ያረፉ 20 አነስተኛ የንግድ ሱቆች ላይ ውድመት ማድረሱን ተናግረዋል፡፡ሁለት ሰዓት በፈጀ አደጋውን የመቆጣጠር ስራ 70 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ ስለመቻሉ አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠር 10 የአደጋ ግዜ ተሽከርካሪዎች፣ 70 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጨምሮ አንድ አንቡላንስ መሰማራታቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡
በትግስት ላቀው