መደበኛ ያልሆነ

ጥር 27፤2014-ሩሲያ በሀሰት ጥቃት ደረሰብኝ በማለት ዩክሬንን ለመውረር እያሴረች ነው ስትል አሜሪካ አስታወቀች

በሩሲያ በሚደገፉ ተገንጣዮች ላይ ወይም ሆን ብላ በራሷ ላይ ጥቃት በመፈፀም የዩክሬይን ጦርን በውሸት ለመወንጀል ሩሲያ መዘጋጀቷን ዋሽንግተን ተናግራለች። ራሷ ሩሲያ ጥቃት ከፈፀመች በኃላ ዩክሬንን ለመውረር ሰበብ እንዲሆናት አቅዳለች ሲሉ የአሜሪካ ባለስልጣናት ገልፀዋል።

ሩሲያ እያጤነች ያለችው አንዱ አማራጭ የውሸት ጥቃትን በመፈፀም ጥዋቱን በምስል ማስረጃ በመቅረፅ ፍንዳታውን የሚያሳዩ መግለጫዎችን ማጋራት እንደሆነም አሜርካ ደርሼበታለሁ ብላለች። በምላሹ ሩሲያ እንዲህ አይነት እቅድ እንደሌላት አስተባብላለች።

በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ያለው የሩስያ ጦር ሃይሎች መብዛት አሜሪካ እና ኔቶን እያሳሰባቸው ይገኛል።ሩሲያ ወታደሮቿ ለሙከራ ልምምድ ላይ መሆናቸውን በመግለፅ ወረራ ለመፈፀም አቅዳለች የሚለውን ክስ ታጣጥላለች።

ይህ ውጥረቱ የመጣው ሩሲያ የዩክሬይንን ደቡባዊ ክራይሚያ ልሳነ ምድርን ወደ ራሷ ከቀላቀለች እና በምስራቅ ዶንባስ ግዛት የተነሳውን ደም አፋሳሽ አመፅ ከደገፈች ከስምንት ዓመታት በኋላ ነው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *