
እ.ኤ.አ. በ1994 በሩዋንዳ ለተፈፀመው የዘር ጭፍጨፋ ዋንኛ የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ ናቸው ተብለው የተከሰሱት ባለሀብት ዘ ሄግ በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ፌሊሰን ካቡጋ በዘር ማጥፋት እና በሰብአዊነት ላይ በፈጸመወ ወንጀሎች የተከሰሰ ሲሆን ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነቱን ክስ ውድቅ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
በቅድመ ችሎቱ ወቅት የአቃቢ ህግ ቡድኑን በመተቸት አዲስ ጠበቃ እንዲሰጣቻው ጠይቀዋል። የ88 አመቱ አዛውንይ ካቡጋ ከሁለት አመት በፊት በፈረንሳይ እስከተያዘቡበይ ጊዜ ድረስ በጣም ከሚፈለጉት የዘር ማጥፋት ተጠርጣሪዎች አንዱ ነበሩ።
የቀድሞው እውቅ ነጋዴ እልቂቱን ለፈጸሙት ሚሊሻዎች ገንዘብ ከፍለዋል በሚል ተከሰዋል። በተጨማሪም ራዲዮ ሚልስ ኮሊንስ የተባለውን የቱትሲ ተወላጆችን እንዲገድሉ የሚያበረታታ የራዲዮ ጣቢያ እንዲቋቋም በገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው በክስ ዝርዝሩ ላይ ቀርቧል።
በሚኪያስ ፀጋዬ