መደበኛ ያልሆነ

ጥር 30፤2014-በስቶኮልም የእየሩሳሌም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አማካይነት ለአጣየ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀዉ የህወኃት ቡድን ከፍተኛ ውድመት ላደረሰበት የአጣየ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በስቶኮልም የእሩሳሌም ወንገላዊት ቤተክርስቲያን ከ495ሺ ብር በላይ የሚያወጡ ሃያ ሰባት ኮምፒውተሮች ፣ሶስት ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር፣ እንዲሁም የኮምፒውተር ቀለሞች እና ሌሎች ለተግባር ትምህርት አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጋቸውን በስቶኮልም የእየሩሳሌም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አስተዳደር የሆኑት ፓስተር ንጉሱ ጉሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

የአጣየ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተደጋጋሚ ውድመት የደረሰበት እንዲሁም ደግሞ አሸባሪው የህውሃት ቡድን አጣየ ላይ በቆየባቸው አስራ አምስት ቀናት ውስጥ እንደ መጠለያ ሲጠቀምበት ቆይቷል፡፡የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ከየትኛውም ተቋም እርዳታ ያላገኝ መሆኑንም የትምህርት ቤቱ ሱፐርቫይዘር አቶ ማሙሽ ሲከፋኝ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

የእየሩሳሌም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አስተዳደር የሆኑት ፓስተር ንጉሱ በቀጣይ የመማር ማስተማሩን ሂደት ሊደግፍ በሚችል መልኩ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡በ1962 ዓ.ም የተመሰረተው ይህ ትምህርት ቤት በርካታ ሙሁራኖችን ያፈራ ነዉ፡፡

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *