መደበኛ ያልሆነ

ጥር 30፤2014-በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ እየተፈጸመ ስላለው መፈንቅለ መንግስት መሪዎች ቅሬታ አሰሙ

ባለፈው አንድ አመት አምስት ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ በአፍሪካ መፈጸሙን ተከትሎ የመፈንቅለ መንግስት ማዕበል ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የተገኙ መሪዎች ቅሬታቸዉን አሰምተዋል፡፡የምርጫ መስፋፋት እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር መኖር በአፍሪካ የመፈንቅለ መንግስት ቁጥር እንዲቀንስ አድርጎ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

የጦር ሰራዊት ሀይል በቅርቡ ስልጣን ከተቆጣጠረባቸው ሀገራት መካከል ሁለቱ ቡርኪናፋሶ እና ማሊ አማፂያንን ለመቆጣጠር ሲታገሉ ቆይተዋል።ባለፈው ሳምንት በጊኒ ቢሳው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን የጊኒ ቢሳዉ ፕሬዚዳንት የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ቡድኖች ለመንግስት ግልበጣዉ ሙከራ ተጠያቂ አድርገዋል።

በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በበርካታ ሰዎች ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በጥቅምት አጋማሽ በሱዳን የተካሄደው ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ ግን የሲቪል አገዛዝ ይመለስ በሚሉ በርካታ የጎዳና ላይ ተቃውሞዎችን አስከትሏል። በዚህም የተነሳ ርህራሄ በሌለው ሃይል ከ70 በላይ ሰልፈኞች ተገድለዋል፡፡

በ አዲስ አበባ በተካሄደዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተገኙት እያንዳንዱ መሪ “በማያሻማ መልኩ የታየውን የመንግስት ለውጥ ኢ-ህገ መንግስታዊ በማለት ማውገዛቸውን” የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት መሪ ባንኮሌ አዴዮ ተናግረዋል፡፡ ወታደራዊ መንግስታትን አንታገስም ሲሉ አክለዋል፡፡

ወታደራዊዉን የመንግስት ግልበጣ ተከትሎ ቡርኪናፋሶ፣ጊኒ፣ማሊ እና ሱዳን ከአፍሪካ ህብረት አባልነት መታገዳቸዉ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *