መደበኛ ያልሆነ

ጥር 30፤2014-በኦሃዮ አንዲት እናት የተሰጣቸው የወንድ የዘር ፍሬ በስህተት የባለቤታቸው ሳይሆን የሌላ ሰው መሆኑን ተከትሎ አባት ያሳደጓት የራሳቸውን ልጅ እንዳልሆነ ተሰማ

በኦሃዮ የሚገኙት ጥንዶች እና ሴት ልጃቸው ህክምናዉን የሰጣቸዉን ሀኪም እና የጤና አጠባበቅ ስርዓትን ከሰዋል፡፡ ሐኪሙ በተሳሳተ መንገድ ለእኒሁ እናት የማያውቁት የወንድ የዘር ፍሬ ስፐርም እንደሰጣቸዉ ተረጋግጧል፡፡ጥንዶቹ ማይክ እና ጄኒን ሃርቬይ እ.ኤ.አ 1991 የሚስትን እንቁላል ከባል ስፐርም ጋር በማዳቀል ህክምና ተሳክቶ እናት ጄኒን ፀንሳ ጄሲካ ሃርቪ የተባለ ሴት ልጅን ትታቀፋለች፡፡

ትንሿ ጄሲካ አድጋ ባለትዳር ትሆናለች፡፡ ወደ አውሮጳ ከባለቤቷ ጋር በነበራት ጉዞ የዘረ መል (DNA) ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ይገኛል፡፡ውጤቱም አስደንጋጭ የሆነ ሲሆን ጄሲካን ያሳደጓት ወላጅ አባቷ እንዳልነበር ይደረስበታል፡፡በተጨማሪ ምርመራ የጄሲካ ባዮሎጂካል አባት የመካንነት ህክምና ለማግነት ልክ እንደ ማይክ እና ጄኒን ሃርቬይ በሆስፒታል የተገኙ ሲሆን በወቅቱ በስህተት መቀያየሩ ተደርሶበታል፡፡

ቤተሰቡ በጉዳዩ ላይ ክስ መስርቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *