መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 1፤2014-በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አልፏል

ከጥር 23 እስከ ጥር 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ10 የሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ በሶስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም 10 የንብረት ውድመት ደርሷል፡፡በንብረት ላይ የደረሰዉ ዉድመት በገንዘብ ሲተመን ከሁለት ሚሊየን ሶስት መቶ ሀያ ሺ ብር በላይ እንደሚገመት ተጠቁሟል፡፡

አደጋዎቹ በሰሜን ሸዋ ዉጫሌ ፣ ደገም እና ቅንብቢት ወረዳዎች፣በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሱሉልታ ፣ምስራቅ አርሲ ሊሙ እና ቢልቢሉ ወረዳዎች የደረሱ ናቸው፡:አደጋዎቹ ከንጋቱ 12 ሠዓት እስከ ምሽቱ 6:30 የደረሱ ሲሆን አብዛኞቹ አደጋዎች በከባድ ተሽከርካሪዎች የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የጨመረ ሲሆን ፤ መንስኤዎቹም ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር እና የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *