
የእስራኤል ፖሊስ ፔጋሰስ የተሰኘዉን የስለላ መሳሪያ በመጠቀም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ልጅን ጨምሮ የመብት ተሟጋቾችን እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ እስራኤላውያንን ስልክ ለመጥለፍ ተጠቅሟል ሲል የእስራኤል ጋዜጣ ዘግቧል።በፀረ ኔታንያሁ የተቃውሞ እንቅስቃሴ መሪዎች ላይ ፖሊስ ፔጋሰስን ያለፍርድ ቤት ፍቃድ መጠቀሙን ቀደም ሲል የዘገበው የቢዝነስ ዕለታዊ ካልካሊስት በትላንትናዉ እለት ይህንን ሪፖርት አጋልጧል፡፡
የፖሊስ ኮሚሽነር ኮቢ ሻብታይ በበኩላቸው ለህዝብ ደህንነት ሚኒስትሩ ኦሜር ባሌቭ ክሱን እንዲጣራ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በዳኛ የሚመራ የውጭ እና ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን እንዲቋቋም ጠይቀዋል፡፡ኮሚሽኑ ህገወጥ ነገሮችን ካገኙ በህጉ መሰረት ይታያሉ ሲሉ የፖሊስ ኮሚሽነሩ ሻብታይ መረጃዎች ተከትሎ በትላንትናዉ እለት በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
በካልካሊስት ይፋ የተደረገዉ የፖሊስ የስለላ ድርጊት የወቅቱ የፖሊስ ኮሚሽነር ከመሾማቸዉ በፊት ነበር፡፡ፔጋሰስ በስልክ ካሜራ ወይም ድምጽ መረጃን መሰብሰብ የሚችል በእስራኤሉ ኩባንያ NSO የሚሰራ የስለላ ቴክኖሎጂ ነዉ፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ