መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 2፤2014-የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሞይ የልጅ ልጅ የቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸው ከቤት ተባረሩ

የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት የነበሩት የዳንኤል አራፕ ሞይ የልጅ ልጅ በስድስት ወራት ውስጥ ከ2,100 ዶላር በላይ የተጠራቀመ የቤት ኪራይ ክፍያ መክፈል ባለመቻላቸዉ ከቤት መባረራቸዉ ተሰምቷል፡፡የሞይ ዘመዶች በቤተሰብ ሀብት አስተዳደር ዙሪያ በፍርድ ቤት የይገባኛል ክርክር ላይ ይገኛሉ፡፡

የ45 አመቱ ኮሊንስ ኪቤት የቤት ኪራይ መክፈልም ሆነ ቤተሰቡን ማስተዳደር እንዳልቻለ ለፍርድ ቤት በመግለጽ ባለፈው ሳምንት ከመኖሪያ ቤታቸው ክፍያ መፈጸም ባለመቻሉ እንደተባረሩም ተናግረዋል።የእንጀራ እናታቸዉን ጨምሮ ዘመዶቻቸዉን የወላጅ አባቴን ሀብት እንዳልወርስ አግደዉኛል ሲሉ ከሰዋል።

የሞይ ልጅ ጆናታን ቶሮይቲች ኑዛዜ ሳይፈጽሙ ከዚህ ዓለም በሞቱ የተለዩ ቢሆንም የቤተሰቡ ሀብት በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል፡፡ሞይ ኬንያን ለረዥም ዓመታት የመሩ ፕሬዝዳንት የነበሩ ሲሆን በ2002 በከፍተኛ ህዝባዊ ግፊት ለ24 አመታትን የሙጥኝ ካሉት ስልጣን ወዉረዳቸዉ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *