መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 4፤201-በአዳማ ከተማ በኮንትሮባንድ መድሀኒት ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በአዳማ ከተማ መስተዳድር ዳቤ ክፍለ ከተማ በዳኔ ሹሉቄ ቀበሌ ልዩ ቦታው ኤላ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በኮንትሮባንድ መድሀኒት ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጥተዋል፡፡

ተከሳሽ በረከት በሀይሉ እና ታሪኩ ብርሀኑ የተባሉ ግለሰቦች ሹፌር እና ረዳት ሲሆኑ ከሀረር ከተማ ወደ አዳማ በተለምዶ ዶልፊን በሚባለዉ ተሸከርካሪ በሁለት ካርቶን በርካታ መድሀኒቶች እና 20 ጥቅል ሺቲ ይዘው ሲጓዙ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መያዛቸው ተገልፆል፡፡

በሰዓቱም ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለው የክስ መዝገባቸው ተጣርቶ ለአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይቀርባል ።ፍ/ቤቱም የቀረበበትን የክስ መዝገብ ከመረምረ በኋ ላ አንደኛ ተከሳሽን በ2 ዓመት ሁለተኛ ተከሳሽ ደግሞ በ2 ዓመት ከ6 ወር እስራት እዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡

የተያዘው መድሀኒት እና አልባሳት ለአዳማ ከተማ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገቢ መደረጉን የከተማው አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነትና ከፍተኛ ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *