መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 4፤201-የአሜሪካ ዜጎች ዩክሬንን ለቀው እንዲወጡ ጆ ባይደን ጥሪ አቀረቡ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዩክሬን የቀሩ አሜሪካዊያን በሙሉ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል::ሩሲያ የምታደርገዉ የወታደራዊ እርምጃ ስጋት እየጨመረ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ጽህፈት ቤት በዩክሬን የሚገኙ አሜሪካውያን በአስቸኳይ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ባይደን ለኤንቢሲ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አሜሪካውያን ዜጎች አሁኑኑ ለቀዉ መዉጣት አለባቸው ብለዋል።

ባይደን ሞስኮ ዩክሬንን ከወረረች አሜሪካውያንን ለመታደግ ጦር አልልክም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ነገሮች በፍጥነት ሊቀያየሩ ይችላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በድንበሯ ላይ ከ100,000 በላይ ወታደሮቿን ብታሰፍርም ዩክሬንን ለመውረር እቅድ የለኝም ስትል ደጋግማ ታስተባብላለች፡፡

ሞስኮ የቀድሞዋ የሶቪየት ህብረትና የወቅቱ ጎረቤቷ የሆነችዉ ዩክሬን ኔቶን እንደማትቀላቀል ቀይ መስመር እንደሆነ እንዲታወቅ ትፈልጋለች፡፡ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን በበኩላቸዉ በትላንትናዉ እለት በአውሮጳ በአስርተ አመታት ውስጥ ያልታየ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ችግር አጋጥሟል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *