መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 4፤201-4ታንዛኒያ የቀድሞ የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ይተቹ የነበሩ ጋዜጦች ላይ የጣለችዉን እገዳ አነሳች

የታንዛኒያ ሟቹ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ታግደዉ የነበሩ አራት ጋዜጦች ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ አንስታለች። ምዋናሃሊሲ፣ ማዊዮ፣ ማሴቶ እና ታንዛኒያ ዳይማ የተባሉት ጋዜጦች ሀሰተኛ መረጃን ማነፈስ በሚል እና በተለያዩ ምክንያቶች ታትመዉ እንዳይሰራጩ ፍቃዳቸው ታግዷል።

እ.ኤ.አ በ2015 እና በ2020 በድጋሚ ምርጫ በማሸነፍ ስልጣን የተረከቡት ማጉፉሊን በመተቸት የሚታወቁት ጋዜጦች እንዲታገዱ መደረጋቸዉ ይታወሳል፡፡ባለፈዉ ዓመት በመጋቢት ወር የማጉፉሊን ህልፈት ተከትሎ ወደ ስልጣን የወጡት ፕሬዝደንት ሳሚያ ሱሉሁ የሚዲያ ነፃነትን ለማስከበር ቃል ገብተዋል፡፡

ተንታኞች እንደሚሉት ዉሳኔዉ በታንዛኒያ የሚዲያ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ መምጣቱን ያሳያል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡እገዳዉ መነሳቱን ተከትሎ የመዋሃሊሲ እና ሙሴቶ ጋዜጣ ባለቤቶች ፕሬዝዳንት ሳሚያን በማመስገን በሥነ ምግባር እና በሚዲያ ህግ መሰረት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *