መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 8፤2014-በሱዳን በቀጠለው ተቃውሞ ሁለት ሰልፈኞች በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው ተሰማ

በሱዳን የሚገኙ የዶክተሮች ማህበር በትላንትናዉ እለት ሁለት ሱዳናውያን ሰልፈኞች በጸጥታ ሃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው መገደላቸዉን ማህበሩ በዛሬዉ እለት ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡ይህም በወታደራዊዉ ሀይል ከተመራዉ የጥቅምት መፈንቅለ መንግስት ወዲህ የተገደሉትን ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 80 አድርሶታል።

ወታደራዊ አገዛዝ ስልጣኑን እንዲያስረክብ ለማድረግ እና በቅርቡ የታሰሩ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ የዲሞክራሲ ደጋፊዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የተቃዉሞ ሰልፍ ማካሄዳቸዉን ቀጥለዋል፡፡ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአንድ ወቅት በገዥው ሉዓላዊ ምክር ቤት ውስጥ የነበሩ ሶስት ፖለቲከኞች ታስረዋል።

ካለፈው ሳምንት አንስቶ በአንድ ወቅት በገዥው ሉዓላዊ ምክር ቤት ውስጥ አባል የነበሩ ሶስት ፖለቲከኞች ታስረዋል።ግለሰቦቹ በቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ለሶስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ የስልጣን ዘመን የተዘረጋውን ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትስስር ለማፍረስ የተሾመ ግብረ ሃይል አባልም ነበሩ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *