መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 8፤2014-በቀሌም ወለጋ የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር ሁለት አምቡላንሶች እንደተወሰዱበት አስታወቀ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የቄለም ወለጋ ቅርንጫፍ ንብረት የሆኑና ማኅበሩ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው ሁለት አምቡላንሶች በግዳጅ እንደተወሰዱበት ገልጿል፡፡

ብስራት ሬድዮ ከማህበሩ ባገኘው መረጃ መሰረት የታርጋ ቁጥር ET05-02121 እና ታርጋ ቁጥር ET05-02108 አምቡላንሶቹ ሰሞኑን በቄለም ወለጋ ለሰብዓዊ አገልግሎት ሲንቀሳቀሱ ማህቡ በውል ባላወቀበት ሁኔታ በግዳጅ እንደተወሰዱበት አስታውቋል ፡፡

ድርጊቱ ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ኮንቬንሽን የሚፃረርና፣ ከማህበሩ ዓላማ ውጪ መሆኑን የገለጸው ቀይ መስቀል፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አምቡላንሶቹን ወደ ማህበሩ ተመልሠው ለህብረተሠቡ የተለመደውን ሰብዓዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲሰጠን ሲል ጠይቋል።

ናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *