መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 8፤2014-ተማሪዉን በመግረፍ ለሞት ዳርጓል የተባለዉ አስተማሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

በናይጄሪያ ውስጥ አንድ የትምህርት ቤት መምህር የ19 ወር እድሜ ያለዉን የቅድመ ትምህርት ቤት ተማሪን በመግረፍ ገድሏል በሚል በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታዉቋል።በአሳባ ፣ ዴልታ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የመዋእለ ሕጻናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪው ባለፈው ሰኞ በህጻኑ አካል ላይ በፈጸመዉ ቅጣት ቁጥሩ በርከት ያለ ምልክት በህጻኑ ሰዉነት ላይ እንዲወጣ አድርጓል፡፡

ቅጣቱን የፈጸመዉ መምህር የግል ትምህርት ቤቱ ባለቤት ልጅ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን ተማሪው በውሃ ሲጫወት በመያዙ መደብደብ እንደጀመረ ተነግሯል።ስለፈጸመዉ ድርጊት የሰጠው አስተያየት የለም።ተማሪው ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ ታሞ እንደነበርና ወደ አሰብ ወደ ፌደራል ህክምና ተወስዶ ህክምና ቢደረግለትም በስተመጨረሻ ህይወቱ አልፏል።

የፖሊስ ቃል አቀባይ ዲኤስፒ ዳፌ ብራይት ለቢቢሲ ፒድጂን እንደተናገሩት ተጠርጣሪው በግድያ ወንጀል ክስ ይመሰረትበታል ብለዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *