መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 9፤2014-ሩሲያ በዩክሬን ላይ አሁንም ጥቃት ልትፈጽም ትችላለች ሲሉ ባይደን ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንደተናገሩት ሩስያ በዩክሬን ላይ አሁንም ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል በመግለጽ ሊደርስ የሚችለዉ ሰብዓዊ ኪሳራ እጅግ ግዙፍ ነዉ ሲሉ አስታዉቀዋል፡፡በአገር አቀፍ ደረጃ በቴሌቪዥን በተላለፈው የፕሬዝዳንቱ መልዕክት ዩናይትድ ስቴትስ ለእንደዚህ ዓይነቱ እርምጃ ቆራጥ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በሚያዋስናት ድንበር 150,000 ወታደሮችን አስፍራለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ አንዳንድ ሃይሎች አካባቢዉን ለቀዉ መውጣታቸውን ቢያሳዉቅም ባይደን ግን ይህ አልተረጋገጠም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ባይደን የሩሲያ ጦር መልቀቅ ጥሩ ነበር ነገርግን እስካሁን አላረጋገጥንም ሲሉ አክለዋል፡፡

ባይደን ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሞስኮ የጸጥታ ስጋት ትኩረት ሊሰጠው እና በቁም ነገር መታየት እንዳለበት ከተናገሩ ከሰዓታት በኋላ ነው።ፑቲን በተደጋጋሚ ዩክሬንን ለመዉረር አቅደዋል መባሉን ያስተባብላሉ፡፡ ፣ ሩሲያ በአውሮጳ ምድር ሌላ ጦርነት ሀገራቸዉ እንደማትፈልግ ቢናገሩም ከህዳር ወር ጀምሮ ያለዉ ውጥረት ግን እየጨመረ ይገኛል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *