መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 9፤2014-በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ትክክለኛ እርምጃ ነው ስትል ቱርክ ተናገረች

በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ትክክለኛ እርምጃ ነው ስትል ቱርክ ገለጸች፡፡
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ÷ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን አገሪቱ በበጎ ጎኑ እንደምታየውና እንደምትቀበለው አስታውቋል።
ውሳኔው በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የሚያስችል ትክክለኛ እርምጃ እንደሆነ ቱርክ እንደምታምንም ተመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የሚደረጉ ሁሉንም ጥረቶች መደገፏን እንደምትቀጥልና ለስኬታማነቱም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትሰራለች ሲል የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ፡፡

ኢዜአ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *