
ከከፍተኛ የስራ እጦት ጋር ስትታገል የቆየችዉ አልጄሪያ መንግስት ለወጣቶች የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞችን እንደሚተገብር የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቦኔ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት እድሜያቸዉ ከ19 እስከ 40 ዓመት ለሆኑ ሥራ ፈላጊዎች ከመጋቢት ወር አንስቶ መንግስት ክፍያ መፈጸም እንደሚጀምር አስታዉቀዋል።
ለስራ ብቁ የሆኑ ሰዎች ሥራ እስኪያገኙ ድረስ በየወሩ ወደ 100 ዶላር ክፍያ እንዲሁም አንዳንድ የሕክምና ጥቅማጥቅሞችን ማግኘት ይችላሉ፡፡ይህንን መሰል ጥቅም በማስተዋወቅ ከአውሮጳ ሀገራት ውጪ ተግባራዊ በማድረግ አልጄሪያ የመጀመሪያዋ ሀገር መሆኗን ፕሬዝዳንት ቴቦዩን ተናግረዋል፡፡
በአልጄሪያ ከ600,000 በላይ ስራ አጦች እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በስምኦን ደረጄ