
በኬንያ መዲና ናይሮቢ ከሶስት ወራት በፊት የታገተውን ኢትዮጲያዊ ባለሀብት አቶ ሳምሶን ተክለማርያም ጉዳይን በተመለከተ በቅርቡ እልባት እንደሚየገኝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።አምባሳደር ዲና በዛሬው እለት ሳምንታዊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ ማብራሪያ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
በኬንያ የታገተውን ሳምሶን ተክለማርያን በተመለከተ በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን የማጣራት ስራ ላይ ይገኛል።ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት መካሄዱን እና በቅርቡ እልባት እንደሚያገኝ እናምናለን ሲሉ አምባሳደር ዲና መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
አቶ ሳምሶን ተክለሚካኤል በኬንያ ኑሮውን ያደረገ ባለሀብት ሲሆን ከሶስት ወር ገዳማ በፊት በናይሮቢ ኬሌሌሽዋ የሚባል መንገድ ላይ የኬኒያ ፖሊስ የደንብ ልብስ የሚመስል በለበሱ ሰዎች ከሚያሽከረክረው መኪና ላይ ኃይል በመጠቀም በማስወረድ የያዘውን ሰነድና ንብረት በመወስድ ሲያግቱት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
ሆኖም ግን አሁንም ድረስ ያለበት እንደማይታወቀ የሚነገሩት ቤተሰቦቹ በወንጀል ይፈለግ ከሆነም በአግባቡ ይዳኝልን ሲሉም ጠይቀዋል ፡፡ቤተሰቦቹ የኬንያ መንግስት ይፈልገው እንደሆነ መጠየቃቸውን የተናገሩ ቢሆንም በምንም አይነት ወንጀል የኬንያ መንግስት እንደማይፈልገው የሚያሳይ ወረቀት እንደተሰጣቸውም ገልፀዋል ፡፡ እስካሁን በህይወት መኖሩ አልያም ህይወቱ ማለፉን የምናውቀው ነገረ የለም ፍትህ እንፈልጋለን ሲሉ ለብስራት ሬዲዮ መናገራቸው ይታወሳል።
በቤቴልሄም እሸቱ